You cannot register for this webinar
This webinar has ended. Thank you for your interest.
Topic
ፀረ ኢትዮጵያና ፀረ አማራ ትርክቶች መቸና እንዴት ተጀመሩ? ይህ በውጭ ሃይሎች የተቀነቀነው የተሳሳተ ትርክት በሀገር በቀል ሃይሎች ተግባራዊ ሊሆን እንዴት ቻለ?
Date & Time
Selected Sessions:
Oct 14, 2023 02:00 PM
Description
ፀረ አማራና ፀረ ኢትዮጵያ ትርክቶች መንሳኤዎች፣ የውጭና አገር-በቀል አቀንቃኞች ሚና፣ ያስከተሏቸው መዘዞችና መፍትሔዎቻችው፣
የኢትዮጵያዊነት የዜጎች መብት ማስከበሪያ ጉባዔ "የአማራን ሕዝብ በጨቋኝነት የመሳል የሃሰት ትረካዎች ምንጭ፣ የውጪና የውስጥ አቀንቃኞች ሚና፤ የሃሰት ትረካው ያስከተሏቸው መዘዞችና ፤ ከነዚህ ምን እንማራለን፤ እንዳይደገምስ ምን የመፍትሄ ሃሣብ እናቀርባለን" በሚሉ ርዕሶች፣ በሦስት ተከታታይ ዌቢናሮች እንደሚያቀርብ በታላቅ ደስታ እየገለፀ፤ በመመዝገብ ተሳታፊ እንድትሆኑ በአክብሮት ይጠይቃል።
የአማራና አማርኛ-ተናጋሪ የሆነውን ማሕበረሰብ አሁን የገጠመው ቀውስ እንዲሁም በሃገሪቱ ላይ በሰፊው ሰፍኖ ሕዝቡን ለማያባራ ችግር የዳረገው፤ ለረጅም ጊዜ የዘለቁት የሃሰት ትርክቶች ከየት እንደመንጩ የግንዛቤ ስምምነት አለ። እነዚህ የሃሰት ትረካዎች መጀመሪያ በ19ኛው ክፍለ ዘመን በቅኝ ገዢዎች የተቀነቀኑ ሲሆን፤ ዓላማውም የኢትዮጵያንና የአማራን ሕዝብ አይበገሬነትና ለነጻነቱ ቀናኤነት ገንዘቡ ያደረገውን ማንነት ለማንኳሰስና ለማሳነስ የተቃጣ ነበር።
በቀጣይ የሃሰት ትርክቱ፤ ከ1950ዎቹ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ የዘለቀና በተለይም፤ በአንዳንድ ግራ-ዘመምና ጎሰኝነትን በሚያራምዱ ነገር ግን ራሳቸውን ለሥልጣን ተረካቢነት እጩ ያደረጉ ልሂቃንን ጨምሮ በተለያዩ ተዋናዮች ሲገፋ ቆይቷል።
የአማራ ሕዝብ እንደ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሁሉ በተከታታይ በተነሱ መንግስታት ከባድ አገዛዝ ሥር የየተጨቆን አማራ የኢትዮጵያ የሕዝብ ጠላት እንደሆነ የተገፋው የሃሰት ትርክት ለከባድ አደጋ ኢላማ እንዲሆን አድርጎታል። ይህ ትረካ እንደ EPLF, TPLF, እና OLF የመሳሰሉ አገር-በቀል የጎሳ ነፃ አውጭና ነጻነት እንቅስቃሴዎች መጀመሪያ ላይ ድጋፍ ለማሰባሰብ፣ በኋላም የፖለቲካ ስልጣንን ለማግኘት ተጠቅመውበታል።
የሀሰት ትርክቱ ምንጭ በውጭ አገርም የተገፋ ቢሆንም፣ በአገር ውስጥ ከፍተኛ መዘዝ አስከትሏል። የትርክቱ አራማጆች በአንፃሩ የፖለቲካ ግባቸውን ሲያሳኩ፤ የአማራ ሕዝብ ግን ለግድያ፤ ለመፈናቀል፣ ቀየው ለማያባራ የአመጽና፤ የንብረት ውድመት ዒላማ ሆኖ ቀጥሏል።
የእነዚህን የሀሰት ትርክቶች ምንጮችና በአማራ ሕዝብ እና በኢትዮጵያ ላይ አሉታዊ መዘዞች በጥናታዊ-ምርምር ለመረዳት፣ ለማጋለጥና ለሰፊው ማሕበረሰብ ግንዛቤ ለማስጨበጥ፣ በቅዳሜ ኦክቶበር 14፣ በኦክቶበር 21 እና በኦክቶበር 28 ፣ 2023 ባሉት ሶስት ተከታታይ ቅዳሜዎች በሦስት የአስተምርሆት ፕሮግራም ይቀርባል ።
ዌቢናር 1 የታሪክ አመጣጥ እና መንስኤዎች
ጥቅምት 14 ቀን 2023 ዓ.ም በዚህ ተከታታይ ርዕስ የሐሰት ትርክቱ ታሪካዊ መነሻ፣ ከቅኝ ግዛት ኃይሎች ጋር ያለውን ግንኙነትና የዓድዋ ጦርነትን እንመርምራለን። እንደ EPLF፣ TPLF እና OLF ያሉ የነጻነት እንቅስቃሴዎች አማሮችን ጨቋኞች አድርገው በማጥቃት እና ተከታዮቻቸውን ለማሰባሰብ የተጫወቱትን ሚናም እንቃኛለን።
ዌቢናር 2 ያስከተለው መዘዝና እና ጉዳቶች
ጥቅምት 21 ቀን, 2023 ዓ.ም በዚህ ተከታታይ ርዕስ በዘለቄታው የሃሰት ትርክቶች ምክንያት በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ የአማራ ሕዝብ የደረሰባቸውን አውዳሚ መዘዝና የማይሰላ ጉዳት ይመረመራል።
ዌቢናር 3 ከዚህ ምን እንማራለን እና የመፍትሄ ሃሣቦች
ጥቅምት 28, ቀን 2023 ዓም የመጨረሻው ተከታታይ ርዕሳችን በመፍትሔ ላይ ያተኮሩ ውይይቶችን የሚካፈሉ አራት ታዋቂ ባለሙያዎችን ያቀርባል።
ለምዝገባና ተጨማሪ መረጃ በ www.ethiopiawinnet.com ድረ ገፃችንን ይመልከቱ።